Fana: At a Speed of Life!

የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ አሳታፊና አካታች ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ እየተደረገ ያለውን ጥረት አደነቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 15፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውሮፓ ኅብረት የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አሳታፊ እና አካታች ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ እያደረገ ያለውን ጥረት አደነቀ፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እና በአውሮፓ ኅብረት የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ከፍተኛ ልዑክ ውይይት አድርገዋል፡፡

በውይይቱ ላይም በኢትዮጵያ እየተካሄደ የሚገኘውን የሀገራዊ ምክክር ሂደት በተመለከተ ለልዑኩ ገለጻ ተደርጓል፡፡

ኮሚሽኑ እያከናወናቸው ያሉ ተግባራት እና በሂደቱም ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በገለጻው ላይ ተነስተዋል፡፡

የልዑካን ቡድኑ መሪ እና የኅብረቱ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ልዩ ተወካይ ኤመን ጊልሞር ÷ ኮሚሽኑ በኢትዮጵያ አሳታፊ እና አካታች ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ እያደረገ ያለው ጥረት አድናቆት የሚቸረው ነው ብለዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.