Fana: At a Speed of Life!

ኦሞ ኩራዝ ቁጥር 2 ስኳር ፋብሪካ ጥገናው ተጠናቅቆ  ማምረት ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካ ዓመታዊ የአጠቃላይ ጥገና እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎቹን በማጠናቀቅ ምርት ማምረት መጀመሩ ተገለጸ፡፡

ፋብሪካው በበጀት ዓመቱ በ3 ሺህ 600 ሔክታር ላይ የለማ የሸንኮራ አገዳን በግብዓትነት በመጠቀም 151 ሺህ 200 ኩንታል ስኳር እንደሚያመርት ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም ከ8 ሺህ 402 ቶን በላይ ሞላሰስ እና ሌሎች ተረፈ ምርቶችን ለማምረት አቅዶ ወደሥራ መግባቱን የኢትዮጵያ ስኳር ኢንዱስትሪ ግሩፕ መረጃ ያመላክታል፡፡

የ2016 በጀት ዓመት ዕቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ ዓመታዊ የአጠቃላይ ጥገና እና ሌሎች የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን በማጠናቀቅም በቅርቡ ወደምርት መግባቱ ነው የተገለጸው፡፡

ፋብሪካው በ2015 የምርት ዓመት 88 ሺህ 720 ኩንታል ስኳር ማምረቱ ይታወሳል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.