Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ በትጋት የሚሠራ ዲፕሎማሲን ይሻል – የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ አሁን ላይ ያለችበት ሁኔታ በትጋት የሚሠራ ዲፕሎማሲን እንደሚጠይቅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) አስገነዘቡ፡፡

አምባሳደር መለስ (ዶ/ር) ዛሬ በሰጡት መግለጫ÷ ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል እና በጋራ ተጠቃሚነት መርኅ የምትሠራውን የመልማት ተግባር በጠንካራ ዲፕሎማሲ እንደምትቀጥል አስታውቀዋል፡፡

በቀጣናው በጋራ እንልማ ብሎ ለመጣ ሀገርና አካል ሁሉ ለመወያየትና ለድርድር ዝግጁ መሆኗንም በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡

ከፍትሐዊነት ውጭ ከየትኛውም አካል ሁኔታዎችን ለማጋጋል የሚወጡ መግለጫዎች ለማንም የማይጠቅሙ እና ለውጥ የማያመጡ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡

በሌላ በኩል የአፍሪካ ኅብረት ስብሰባን በተለመደው ሁኔታ በተሳካ መንገድ ለማከናወን ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ መገባቱን ጠቅሰዋል፡፡

መንግሥት ከሚያከናውናቸው ሥራዎች በተጨማሪ ኅብረተሰቡም የሚጠበቅበትን እንዲወጣ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በሣይንስ ሙዚዬም በመካሄድ ላይ የሚገኘው የዲፕሎማሲ ሣምንትም÷ በተቋማት፣ ዲፕሎማቶችና ማኅበረሰቡ እየተጎበኘ መቀጠሉን በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

 

በፍሬሕይወት ሰፊው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.