ቢዝነስ

ክልሉ ከ14 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ አቀረበ

By Mikias Ayele

January 25, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተጠናቀቀው ግማሽ ዓመት ከ14 ሺህ ቶን በላይ የቅመማ ቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ማቅረቡን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል አስታወቀ፡፡

ለማዕከላዊ ገበያ ከቀረቡት መካከልም ከፍተኛውን ድርሻ የሚይዙት÷ ዝንጅብል፣ ዕርድ፣ ቁንዶ በርበሬ እና ኮረሪማ መሆናቸውን የክልሉ ቡና፣ ሻይ እና ቅመማ ቅመም ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አሥራት መኩሪያ ተናግረዋል፡፡

የቅመማ ቅመም ምርቶች ዋጋ መሻሻል እና የአምራች አርሶ አደሮች ግንዛቤ ማደግ ከፍተኛ ምርት ለማምረት መልካም አጋጣሚ ሆኗል ብለዋል፡፡

በቀጣይም የቅመማ ቅመም ምርትን ማሣደግና የገበያ ትስስር መፍጠር ላይ በትኩረት እንደሚሠራ ጠቁመዋል፡፡

በበጀት ዓመቱ ከ54 ሺህ ቶን በላይ የቅመማቅመም ምርት ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መታቀዱንም ጠቅሰዋል፡፡