75 ኢትዮጵያውያን ከጅቡቲ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በጅቡቲ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 75 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል፡፡
በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በሀገሪቱ ከሚገኘው የዓለም አቀፍ ፍልሰተኞች ድርጅት ጋር በመተባበር ነው ኢትዮጵያውያኑ ወደ ሀገራቸው የተመለሱት፡፡
የጅቡቲ-የመን መንገድ እጅግ አደገኛ ከመሆኑም በላይ በየቀኑ የብዙዎችን ሕይወት እያሳጣ እንደሚገኝ ኤምባሲው ጠቁሟል፡፡
ዜጎች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ከዚህ አደጋ እንዲቆጥቡ እና የጸጥታ እና ሌሎች ተቋማትም ሃላፊነታቸውን እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!