አቶ ደመቀ ከዩኒሴፍ የምሥራቅና ደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ጋር መከሩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከዩኒሴፍ የምሥራቅ እና ደቡብ አፍሪካ ቀጣናዊ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይታቸውም ፥ በቀጣይ ከዩኒሴፍ ኢትዮጵያ ጋር በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
ለችግር የተጋለጡ ሕጻናትን እና ቤተሰቦቻቸውን ከድህነት ለማውጣት ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም አቶ ደመቀ በአጽንኦት ገልጸዋል፡፡
ዩኒሴፍ በተለይም ለችግር ተጋላጭ ህጻናት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አድንቀዋል።
ድርጅቱ በግጭት እና በአየር ንብረት ለውጥ ጉዳት ለደረሰባቸው ሕዝቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያሳድግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዳይሬክተሯ በበኩላቸው ፥ በአሁኑ ወቅት ዩኒሴፍ በኢትዮጵያ በግጭት እና በአደጋ ለተጎዱ ህጻናት ሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አንስተዋል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!