2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን በመዲናዋ የተለያዩ ሥፍራዎችን እየጎበኙ ነው
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተቀብለው ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ሁለተኛው ትውልድ ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ የተለያዩ ሥፍራዎች ጉብኝት እያደረጉ ነው።
ጉብኝቱ በቱሪዝም ሚኒስቴር፣ በኢትዮጵያ አየር መንገድ እና በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት ትብብር የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ጎብኝዎቹ የዓድዋ ዜሮ ዜሮ ፕሮጀክት፣ ብሔራዊ ሙዚዬምን እና እንጦጦ ፓርክን እንደሚጎበኙ ተገልጿል።
የጉብኝቱ ዋና ዓላማ በተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ 2ኛ ትውልድ ኢትዮጵያውያን የሀገራቸውን ባህልና ታሪክ እንዲያውቁ እና ትስስራቸውን ይበልጥ እንዲያሳድጉ ለማስቻል እንደሆነም ተመላክቷል፡፡