የአውስትራሊያ ብሔራዊ ቀን በአዲስ አበባ ተከበረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 16፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የአውስትራሊያ ብሔራዊ ቀን በአዲስ አበባ በሚገኘው የሀገሪቱ ኤምባሲ ተከብሯል፡፡
በመርሐ ግብሩ የኢትዮጵያ መንግስትን በመወከል የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ በክብር እንግድነት ተገኝተው የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ሚኒስትሯ በመልዕክታቸው ፥ ቱሪዝምን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች በሀገራቱ መካከል ያለው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ቁርጠኛ መሆኗን አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ የአውስትራሊያ አምባሳደር ጁሊያ ኒብሌት በበኩላቸው ፥ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት አጋርነት ረጅም ዘመናትን አንዳስቆጠረ አውስተዋል፡፡
በቀጣይም በተለይ በኢኮኖሚ ያላቸው ትስስር እንዲጠናከር የሚያስችሉ ሥራዎች እንደሚሰሩ ማረጋገጣቸውን የቱሪዝም ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!