የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን 715 ሚሊየን ብር አተረፈ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የግብርና ሥራዎች ኮርፖሬሽን ባለፉት ስድስት ወራት 5 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታውቋል፡፡
የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ክፍሌ ወ/ማርያም እንዳሉት÷ ኮርፖሬሽኑ ባለፉት ስድስት ወራት 4 ቢሊየን 777 ሚሊየን ብር ገቢ ለማግኘት አቅዶ 5 ቢሊየን 580 ሚሊየን ብር አግኝቷል።
ኮርፖሬሽኑ ከታክስ በፊት 715 ሚሊየን ብር ማትረፉን ጠቁመው÷ ይህም ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ በሁሉም የሥራ ዘርፎች የተሻለ አፈጻጸም ለማስመዝገብ በቅንጅት እንደሚሰራ መናገራቸውንም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡