አየር መንገዱ ወደ ጃፓን የሚያደርገው ሳምንታዊ በረራ ወደ 7 ከፍ እንዲል ተወሰነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) ኢትዮጵያና ጃፓን ቀደም ሲል ሲሰሩበት የነበረውን የአየር ትራንስፖርት ስምምነት አሻሽለዋል፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን እና በጃፓን ዓለም አቀፍ የአየር ትራንስፖርት ክፍል የሲቪል አቪዬሽን ቢሮ የሥራ ኃላፊዎች በበይነ መረብ ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸወም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ጃፓን የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ከአምስት ወደ ሰባት ማሳደግ እንዲችል ተስማምተዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቀደም ሲል አምስተኛ የትራፊክ መብትን በመጠቀም በሁለቱ ሀገራት መሀከል የነበረው የበረራ ስምምነት ገደብ እንዲነሳ መደረጉ ተጠቅሷል፡፡
ቀደም ሲል በነበረው ስምምነት መሰረት የኢትዮጵያ አየር መንገድ 50 በመቶ የመጫን አቅምን ብቻ መጠቀም ይችል እንደነበር ተጠቁሟል፡፡
አሁን በተደረገው ስምምነትም ይህ ገደብ እንዲነሳ ስምምነት ላይ መደረሱን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለስልጣን መረጃ ያመላክታል፡፡
እስካሁን ከጃፓን ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ ምንም አይነት በረራ የሌለ ሲሆን÷ ወደፊት የሚጀመር ከሆነ ግን ስምምነቱ ለጃፓንም የሚሰራ ይሆናል