ስደተኞች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት ለመፍጠር በጋራ መስራት ይገባል – በለጠ ሞላ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ኮርፖሬሽን እና የሶማሌ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከዓለም አቀፍ የስራ ድርጅት ጋር በትብብር ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡
በለጠ ሞላ (ዶ/ር) በዚህ ወቅት እንዳሉት÷ ስደተኞችን እና ተጋላጭ ወጣቶችን ጨምሮ አገልግሎቱ ተደራሽ ያላደረጋቸው ቡድኖች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚሆኑበት ስርዓት ለመፍጠር በጋራ መሰራት ይገባል ብለዋል፡፡
ስደተኞችን የመቀበል ረጅም እና የሚያኮራ ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ ልዩ ቦታ እንዳላት አውስተዋል፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ የቴክኖሎጂ እድገት ፍኖተ ካርታ ብቻ ሳይሆን የዲጂታል አብዮቱ እውነተኛ አቅም ሊከፈት የሚችለው ሁሉንም ሰው የሚያሳትፍ እድል ሲኖረው እንደሆነም አስገንዝበዋል።
የዓለም አቀፍ የስራ ድርጅት ቢሮ ዳይሬክተር እና በአፍሪካ ህብረት እና በኢሲኤ ልዩ ተወካይ አሌክሲዮ ሙሲንዶ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ አሁን ላይ ከ916 ሺህ በላይ ስደተኞችን እያስተናገደች መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡
በዋነኛነት ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ እና ኤርትራ የተወጣጡ ስደተኞች በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ በዲጂታል ኢኮኖሚ መር ልማት ላይ ትኩረት ሰጥታ እየሰራች መሆኑን አውስተዋል።
ይህ ስትራቴጂ የዲጂታል መሠረተ ልማት፣ ትስስር እና ችሎታዎች ለአካታች ዲጂታል ኢኮኖሚ ያለውን ጠቀሜታ የሚያጎላ እንደሆነ መናገራቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!