Fana: At a Speed of Life!

የብልጽግና ፓርቲ ባለፉት ቀናት የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በስፋት መክሯል- አቶ ተመስገን ጥሩነህ

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ የማዕከላዊ እና የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች ባለፉት ቀናት ባካሄዱት ስብሰባ የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ በስፋት መምከራቸውን የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

አቶ ተመስገን ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ባደረጉት ቆይታ በሀገሪቱ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ከሚታዩ አለመረጋጋቶች ውጪ አንጻራዊ ሰላምና ደህንነት መኖሩን ገልጸዋል።

ገዢው ፓርቲ ከታጠቁ አካላት ጋር በህገ መንግስቱ መሰረት ለውይይት በሩ ክፍት መሆኑንም በፓርቲው ስብሰባዎች ላይ መምከሩን አቶ ተመስገን አንስተዋል።

በጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ላይ እየተሰሩ ያሉ የለውጥ ተግባራት በኢትዮጵያ ላይ ከውስጥም ከውጭም የሚቃጡ ትንኮሳዎችን በሚያስቆም ቁመና ላይ እንዲገኙ አስችሏል ብለዋል።

በተለይ ለሀገራቸው እና ለህዝባቸው የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል እያገለገሉ ያሉ የጸጥታ እና ደህንነት ተቋማት ላይ የተለያዩ አካላት የሚያሰራጩትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ለመግታት የብልጽግና ፓርቲ የተለያዩ ስራዎችን መስራት መጀመሩንም ገልጸዋል።

ፓርቲው ባካሄደው ስብሰባ በተለይም በሰላም ጉዳይ ላይ ህዝባዊ ውይይቶች እንዲካሄዱ ውሳኔ ማሳለፉንም የፓርቲው ምክትል ፕሬዚዳንት ተናግረዋል።

 

በምስክር ስናፍቅ
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.