ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና አዳማ ከተማ ድል ቀናቸው

By Melaku Gedif

January 26, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 17፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 1 በማሸነፍ የሊጉን መሪነት አጠናክሯል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን የማሸነፊያ ግቦች ቢንያም ጌታቸውና አዲስ ግደይ ሲያስቆጥሩ÷የባህር ዳር ከተማን ብቸኛ ግብ ደግሞ አለልኝ አዘነ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ አዳማ ከተማ ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!