Fana: At a Speed of Life!

ለስጋ ደዌ ታማሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለስጋ ደዌ ታማሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ እንዲደረግ የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስጋ ደዌ ተጠቂዎች ማህበር ጠየቀ።

ዓለም አቀፍ የስጋ ደዌ ታማሚዎች ቀንን ምክንያት በማድረግ በሐረር ከተማ የእግር ጉዞ ተደርጓል።

በዓለም አቀፍ ለ70ኛ ጊዜ በሀገር አቀፍ ደረጃ 25ኛ ጊዜ “የስጋ ደዌ በሽታን አንዘንጋ” በሚል መሪ ቃል በሐረሪ ክልል በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ ነው።

የበዓሉ አንድ አካል የሆነውና ስለበሽታው ለህብረሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት በሐረር ከተማ የእግር ጉዞ ተካሂዷል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ የስጋ ደዌ ተጠቂዎች ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ከፍያለሁ በቀለ እንደተናገሩት፥ የስጋ ደዌ በፈጣሪ ቁጣ አይመጣም፤ በዘርም አይተላለፍም ብለዋል፡፡

በመሆኑም ለበሽታው ታማሚዎች አስፈላጊው ድጋፍ ቢደረግላቸው እንደማንኛውም ሰው ሰርተው መለወጥ እንደሚችሉም ነው የገለጹት፡፡

ማህበሩም ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በመተባበር የስጋ ደዌ ተጠቂዎች በገቢ ማስገኛ ስራ እንዲሰማሩና ራሳቸውን እንዲችሉ የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በኢትዮጵያ ከ20 ሺህ የሚበልጡ የስጋ ደዌ ታማሚ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚገኙ በዚሁ ወቅት ተገልጿል።

በተሾመ ኃይሉ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.