የኦሮሚያ ባህል ስፖርቶች ውድድርና የባህል ፌስቲቫል በአምቦ ከተማ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 29ኛው የኦሮሚያ ባህል ስፖርቶች ውድድርና 16ኛው የባህል ፌስቲቫል በአምቦ ከተማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
የባህል ስፖርት ውድድሩና የባህል ፌስቲቫሉ ለ15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን 20 ዞኖችና 13 ከተማ አስተዳደሮች ይሳተፉበታል።
በባህል ስፖርት ውድድሩ ላይ ከ1 ሺህ 800 በላይ ተወዳዳሪዎች በ10 የባህል ስፖርቶች ፉክክር ያደርጋሉ።
በሀገር አቀፍ ደረጃ በሚዘጋጀው ውድድር ላይ ክልሉን ወክለው የሚወዳደሩ ስፖርተኞችም ይመረጣሉ።
በከፍያለው ሽፈራው