የጋምቤላና የሲዳማ ክልሎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚቀመጡ ቅርሶችን አበረከቱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የጋምቤላና የሲዳማ ክልሎች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም የሚቀመጡ ቅርሶችን ዛሬ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አበረከቱ።
ክልሎቹ ያበረከቷቸውን ቅርሶች የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ጥላሁን ወርቁ ተረክበዋል።
አቶ ጥላሁን በርክክቡ ወቅት፤ ቅርሶቹ ትውልድ የሚማርባቸው፣ ጎብኚዎችና ተመርማሪዎች የሚመራመሩባቸው መሆናቸውን ገልጸዋል።
ክልሎቹ በመታሰቢያ ሙዝየሙ እንዲቀመጡ ቅርሶቹን ስላበረከቱ በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋና ማቅረባቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል።
ከዓድዋ ድል ጋር የተያያዙ ቅርሶች በዓድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም እንዲቀመጡ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ጥሪ ማቅረባቸው ይታወሳል።