Fana: At a Speed of Life!

በድሬዳዋ 5ጂ የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎት በይፋ ጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በድሬዳዋ የአምስተኛው ትውልድ (5ጂ) የሞባይል ኔትወርክ አገልግሎትን አስጀመረ።

የ5ጂ የሞባይል ኔትወርክን በማስፋፋት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ኢትዮ ቴሌኮም እየተጋ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ አገልግሎቱን በድሬዳዋ ሲያስጀምሩ እንደተናገሩት፤ በአዲስ ፍጥነትና ምቾት የሰው ልጆችን አኗኗር ለማቅለል የተለያዩ ቴክኖሎጂዎች እየተተገበሩ ነው።

5ጂ ከመደበኛው የስልክ ግንኙነት ባሻገር በርካታ መረጃዎችን በፍጥነት ለማስተላለፍ እንደሚያስችል ገልፀው፤ የ5ጂ ቴክኖሎጂ ችግር ፈቺ በመሆኑ ምርታማነትን እንደሚጨምር ተናግረዋል።

የስራ እድል ለመፍጠር ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክትም ዋና ስራ አስፈጻሚዋ አመልክተዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ አቶ ሃርቢህ ቡኽ በበኩላቸው ድሬዳዋ የኢንደስትሪ፣ የንግድና የስልጣኔ መግቢያ በር እንደመሆኗ 5ጂ ቴክኖሎጂ የላቀ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ድሬዳዋ ከ450 በላይ ኢንዱስትሪዎች የሚገኙባት በመሆኑ ፈጣኑ ኔትወርክ ስራን ለማቅለል ያግዛል ብለዋል።

5ጂ ኔትወርክ ከድሬዳዋ ቀደም ብሎ በአዲስ አበባ፣ አዳማና ጂግጂጋ ከተሞች በይፋ የተጀመረ ሲሆን በአጭር ጊዜ ከግማሽ ሚሊየን በላይ ተጠቃሚዎችን ማፍራት መቻሉ በዕለቱ ተገልጿል።

በእዮናዳብ አንዱዓለም

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.