Fana: At a Speed of Life!

ለጋምቤላ ክልል ከ600 ሺህ ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 25፣2012(ኤፍ.ቢ.ሲ) በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የአፍሪካ ቀንድ አካባቢ የልማት ማእከል በጋምቤላ ክልል የኮሮና ቫይረሰ ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ ።

በማዕከሉ ከተበረከቱት ከ600 ሺህ ብር በላይ ግምት ያላቸው የህክምና ቁሳቁሶች መካክል ማይክሮስኮፕ፣ የኦክሰጂን ስሊንደሮች፣ አልጋዎችና ሌሎች ቁሳቁሶች እንደሚገኙበት  ተገልጿል።

የልማት ማዕከሉ ተወካይ አቶ ወንድወሰን ግርማይ ድጋፍን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት÷ ዓላማው ማህበረሰቡ የኮሮና ቫይረስ ለመካለከል በሚያደርገው ጥረት ውስጥ የአጋርነት ሚናችንን ለመወጣት በማሰብ ነው ብለዋል።

አያይዘውም ከልማት በፊት የህዝብ ጤና መቅደም ስላለበት ማዕከሉ በቀጣይም  የጀመረውን ድጋፍ አጠናከሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።

የጋምቤላ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጀሉ  የህክምና ቁሳቁሶችን በተረከቡበት ወቅት እንዳሉት÷ የኮሮና ወርርሽኝ የደቀናቸውን ማህበራዊና ኢኮኖሚዊ ችግሮች ለመሻገር በሚደረገው ጥረት ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና ሊወጡ ይገባል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

#FBC

የዜና ሰዓት ሳይጠብቁ የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬትን ትኩስ እና ሰበር ዜናዎችን በፍጥነት በአጭር የፅሁፍ መልዕክት መልክ በስልክዎ ላይ እንዲደርስዎ ወደ 8111 OK ብለው ይላኩ።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.