Fana: At a Speed of Life!

ፋና በተለያዩ ይዘቶች ያለው ተደራሽነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ኢንስቲትዩቱ የቴክኖሎጂ እገዛ ያደርጋል – ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት በተለያዩ ይዘቶች ያለው ተደራሽነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ እንደሚያደርግ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) ገለጹ፡፡

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ያስገነባውን አዲስ የፋና ላምሮት ስቱዲዮ በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡

በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ አቶ አደም ፋራህን ጨምሮ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ወርቁ ጋቸና (ኢ/ር) በምርቃ ሥነ-ሥርዓቱ ባደረጉት ንግግር÷ የፋና አመራሮች እና ሰራተኞች ዘመናዊ እና ተወዳዳሪ የፋና ላምሮት ስቱዲዮ በመገንባት ለምርቃት በማብቃታችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

ፋና የተለያዩ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቅሞ ከሀገር ውስጥ ብሎም ከዓለም ተወዳዳሪ እንዲሆን ተቋማቸው ዘርፈ ብዙ የቴክኖሎጂ ድጋፍ እንደሚያደረግም ተናግረዋል፡፡

ፋና በይዘት ተደራሽነት፣ በካሜራና ድምጽ ጥራት እንዲሁም በሳቢ አቀራረብ ያለው ተግባር አርዓያ የሚሆን በመሆኑ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አስገንዝበዋል፡፡

በተለያዩ ይዘቶች ፋና ያለውን ተደራሽነት እንዲያስቀጥልና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ተቋም እንዲሆን የተቋሙ ሰራተኞች፣ መንግስት እና ሕዝብ በጋራ እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡

የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መገናኛ ብዙሃን የሚጠበቅባቸውን ሙያዊ ሃላፊነት በሚገባ እንዲወጡ በቅርበት እና በትብብር እየሰራ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

 

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.