ስፓርት

በፕሪሚየር ሊጉ ኢትዮጵያ ቡና ሲያሸንፍ ወላይታ ድቻና ሃድያ ሆሳዕና አቻ ተለያዩ

By Melaku Gedif

January 28, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 19፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የ12ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ዛሬ ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል፡፡

ቀን 9 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ኢትዮጵያ ቡና ወልቂጤ ከተማን 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

የኢትዮጵያ ቡናን ብቸኛ የማሸነፊያ ግብ አንተነህ ተፈራ በ33ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡

በተመሳሳይ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በተካሄደ ጨዋታ ሃድያ ሆሳዕና ወላይታ ድቻን 1 ለ 1 በሆነ ውጤት ተለያይተዋል፡፡