መገናኛ ብዙሀን በሀገራዊ ምክክር ሂደት ግንዛቤ መፍጠር ላይ በስፋት እንዲሰሩ ተጠየቀ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክርን እውን በማድረግ ሂደት መገናኛ ብዙሀን ግንዛቤ መፍጠር ላይ በስፋት እንዲሰሩ ተጠየቀ፡፡
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መስፍን አርአያ(ፕ/ር) እንደገለጹት÷ መገናኛ ብዙሀን በተለያዩ ቋንቋዎች ለህብረተሰቡ ስለ ምክክሩ ሂደት መረጃዎችን ተደራሽ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል።
በርካታ መገናኛ ብዙሀን በምክክሩ የእስካሁን ሂደቶች እና ግንዛቤ መፍጠር ላይ እየሰሩ መሆኑን ጠቅሰው÷ ከዚህ በላይ መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።
ኢትዮጵያ ለገጠሟት ችግሮች በምክክር መፍትሄ ለማበጀት ምክክሩ የሁሉም መገናኛ ብዙሀን አጀንዳ ሊሆን ይገባል ሲሉ ለፋናብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ገልጸዋል፡፡
በዙፋን ካሳሁን