ከ198 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ሆኑ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ባለፉት ስድስት ወራት ከ198 ሺህ በላይ አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡
አገልግሎቱ 265 ሺህ 990 አዳዲስ ደንበኞችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ ነው ለ198 ሺህ 270 አዳዲስ ደንበኞች የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ማድረግ የቻለው፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት የኤሌክትሪክ ሃይል ያገኙ ደንበኞች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻፀር በ56 ነጥብ 58 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱ ተገልጿል፡፡
በግማሽ ዓመቱ የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ከሆኑት ደንበኞች መካከል 95 በመቶው የሚሆኑት የድህረ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ሲሆኑ÷ ቀሪ 5 በመቶ የሚሆኑት ቅድመ ክፍያ ተጠቃሚ ደንበኞች ናቸው ተብሏል፡፡
የአዲስ ሃይል ተጠቃሚ ደንበኞችን ቁጥር ለማሳደግ በተሰራው ስራ የተቋሙን ጠቅላላ ደንበኞች ቁጥር ወደ 4 ሚሊየን 559 ሺህ 345 ማሳደግ እንደተቻለም የአገልግሎቱ መረጃ ያመላክታል፡፡