የሐረሪ ክልል የግማሽ ዓመት አፈጻጸም እየተገመገመ ነው
አዲስ አበባ፣ 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሐረሪ ክልል የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ አጋማሽ የመንግሥትና የፓርቲ የሥራ ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መካሄድ ጀምሯል፡፡
በመድረኩም÷ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ በመደበኛና በካፒታል ፕሮጀክቶች የተከናወኑ ተግባራት እየተገመገሙ ነው፡፡
የግምገማ መድረኩ እስከ ነገ ድረስ እንደሚቀጥል ተገልጿል፡፡
የሐረሪ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ሮዛ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ጌቱ ወዬሳ፣ የሴክተር መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች እና ሌሎች አስፈፃሚ አካላት በመድረኩ እየተሳተፉ ነው፡፡
በተሾመ ኃይሉ