የኢትዮጵያ ወረርሽኝ መከላከል ዝግጁነትና ምላሽ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ ወረርሽኝን ለመከላከልና ምላሽ መስጠት የሚያስችል የ113 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ይፋ ተደርጓል፡፡
በማስጀመሪያ መርሐ ግብሩ ላይ ፥ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፣ የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) እና የዓለም የጤና ድርጅት የቀጣናው ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በቀጣይ ሶስት ዓመታት በተለያዩ አካባቢዎች ተግባራዊ እንደሚደረግ የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
የፕሮጀክቱ ዋነኛ ትኩረትም የላብራቶሪ አቅምን ማሳደግ፣ በጤናው ዘርፍ የቅኝት ስራዎችን ማጠናከር እና የሰው ሃይል ግንባታን ማጠናከር መሆኑ ተገልጿል።
ዶ/ር ሊያ ታደሰ÷በጤናው ዘርፍ የወረርሽኝ መከላከል አቅምን ለማሳደግ እንዲሁም አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ፕሮጀክቱ ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡