Fana: At a Speed of Life!

በኢትዮጵያ 29 የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማእከላት አገልግሎት እየሰጡ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያ 29 የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ማእከላት አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ በሽታ የላብራቶሪ ምርመራ ባለመኖሩ ወደ ደቡብ አፍሪካ ናሙናዎችን እየተላከ ውጤቱን ለማወቅ የጊዜና የገንዘብ ወጪ ያስክትል እንደነበር ያስታወሰው ሚኒስቴሩ፥ ይህን ችግር በመረዳት በአጭር ጊዜ በሀገር ውስጥ የመመርመሪያ መሳሪዎችን በሟሟላት እና ባለሙያዎችን በማሰልጠን የላብራቶሪ ምርመራ ማዕከላትን ማደራጀቱን አስታውቋል።

በአሁኑ ወቅት 29 ማዕከላት የኮቪድ-19 ምርመራ በማድረግ ላይ ሲሆኑ፥ ማእከላቱም እስከ ግንቦት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ለ112 ሺህ 377 ሰዎች የላብራቶሪ ምርመራ አከናውነዋል።

አራት ማእከላት ደግሞ ምርመራውን ለማከናወን የሚያስችላቸውን  ዝግጀት ማጠናቀቃቸውን እና ሌሎች 16 ደግሞ በዝግጅት ላይ መሆናቸውን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

ለመረጃ ይሆን ዘንድ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ19) በሽታ የላብራቶሪ ምርመራ የሚደረግባቸውን ማዕከላት ዝርዝር በክልል እና ከተማ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.