አቶ አደም ፋራህ የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 20፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ አደም ፋራህ የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝት መርሐ ግብሩ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)፣ የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስትር አይሻ መሃመድ (ኢ/ር) እና ሌሎች የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
የምስራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖ “አርብቶ አደርነት የምስራቅ አፍሪካ ኅብረቀለም” በሚል መሪ ሃሳብ ነው በአዲስ አበባ እየተካሄደ የሚገኘው፡፡