Fana: At a Speed of Life!

169 ሺህ 288 ዩኒት ደም ተሰበሰበ

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ አጋማሽ ከበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች 202 ሺህ 509 ዩኒት ደም ለመሰብሰብ ታቅዶ 169 ሺህ 288 ዩኒት መሰብሰቡን የኢትዮጵያ ደም እና ኅብረ-ኅዋስ ባንክ አገልግሎት አስታወቀ፡፡

በደም አሰባሰብ ሂደቱ÷ የመቱ፣ ሻሸመኔ፣ ወሊሶ፣ አዳማ፣ አምቦ፣ ቦንጋ፣ አሶሳ፣ ጅግጅጋ፣ ቢኪ እና ድሬዳዋ ደም ባንኮች የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገባቸው ተገልጿል፡፡

የተሰበሰበው ደም ከዕቅድ አንፃር ጥሩ ሊባል የሚችል ቢሆንም የደም ሕክምና ከሚፈልገው ታካሚ አንፃር ግን በቂ አለመሆኑን የአገልግሎቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሐብታሙ ታዬ ተናግረዋል፡፡

የደም ሕክምና የሚፈልጉ ሰዎች ቁጥር፣ የሕክምና ማዕከላት እና ልዩ ሕክምና የሚፈልጉ በሽታዎች (ለምሳሌ የካንሠር ሕክምና ማዕከላት) በተስፋፉ ቁጥር የደም ፍላጎቱ እንደሚጨምርም አስገንዝበዋል፡፡

ይህን ፍላጎት ለማሟላትም የበጎ ፈቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር ሊያድግ እንደሚገባ ጠቅሰው÷ ሲለግሱ የነበሩም እንዲቀጥሉ፤ ለግሰው የማያውቁም በዚህ ሕይዎት አድን ሥራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

እንደ ሀገር 47 ደም ባንኮች ያሉ ሲሆን ከአንዱ በስተቀር ሌሎቹ በሥራ ላይ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡

በዮሐንስ ደርበው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.