ስፓርት

የሀዋሳ ሃይቅ የግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 3 ይካሄዳል

By Feven Bishaw

January 30, 2024

 

አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 12ኛው የሀዋሳ ሃይቅ የግማሽ ማራቶን ውድድር የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄድ ታላቁ ሩጫ አስታወቀ።

ውድድሩ ከዚህ ቀደም ይታወቅበት የነበረውን ስያሜ በመቀየር “የሀዋሳ ሃይቅ ግማሽ ማራቶን” በሚል ይካሄዳል ነው የተባለው።

በዘንድሮው ውድድር ከወትሮው በተለየ ከእንግሊዝ፣ ከአሜሪካ፣ ጆርጂያ፣ አየርላንድ፣ ጀርመን እና ከሌሎችም ሀገራት የሚመጡ ተሳታፊዎች እንደሚካፈሉ አዘጋጆቹ አስታውቀዋል።

ከሀገር ውጪ ከሚመጡት ተሳታፊዎች በተጨማሪም ከአዲስ አበባ እንዲሁም ሀዋሳ እና አካባቢዋ የሚመጡ ከ3 ሺህ በላይ ተሳታፊዎች በግማሽ ማራቶን፣ በ8 ኪሎ ሜትር እና በህፃናት ውድድር እንደሚሳተፉ ታውቋል፡፡

በሰለሞን በቀለ