ዛሬ “ፀሐይ” አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባችንን የምናከብርበት ቀን ነው – ጠ/ሚ ዐቢይ (ዶ/ር)
አዲስ አበባ፣ ጥር 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ “ፀሐይ” አውሮፕላንን ከጣልያን መንግሥት በይፋ መረከባችንን የምናከብርበት ቀን በመሆኑ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ ታላቅ የኩራት ቀን ነው ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጂኦርጂያ ሜሎኔ ላለፈው አንድ አመት የአውሮፕላኑን መመለስ ስራ በማገዛቸው ለማመስገን እፈልጋለሁ ሲሉም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ ገልጸዋል።
“ፀሐይ” እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ1935 ዓ.ም በጀርመናዊው ኢንጂነር እና የንጉሱ ፓይለት ሄር ሉድዊግ ዌበር ብሎም በወቅቱ በነበሩ ኢትዮጵያዊያን ባለሞያዎች ትብብር በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የተሰራ አውሮፕላን መሆኑንም በመልዕክታቸው ጠቅሰዋል።