የአሜሪካ ተዋጊ አውሮፕላን በደቡብ ኮሪያ መከስከሱ ተሰማ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኤፍ-16 የተሰኘ የአሜሪካ ተዋጊ አውሮፕላን (ጀት) በደቡብ ኮሪያ መከስከሱ ተሰምቷል፡፡
በአካባቢው አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ የአሜሪካ ተዋጊ አውሮፕላን መሰል አደጋ ሲያጋጠመው ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
ተዋጊ አውሮፕላኑ በደቡብ ኮሪያ ጉንሳን ተብሎ በሚጠራ የውሃ አካል ዳርቻ ላይ መውደቁን የአሜሪካ ጦር አስታውቋል፡፡
የመከስከስ አደጋ ያጋጠመው ተዋጊ አውሮፕላኑ በምዕራብ ኮሪያ ልሣነ ምድር በሚገኝ የውሃ አካል ላይ የሥልጠና ተልዕኮ ሲያከናውን እንደነበር ተመላክቷል፡፡
የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት ምርመራ መጀመሩንም ሲ ኤን ኤን በዘገባው አስፍሯል፡፡