Fana: At a Speed of Life!

አደንዛዥ ዕፅ ሲያዘዋውሩ የተገኙ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) አራት ፌስታል አደንዛዥ ዕፅ በተሽከርካሪ ጭነው ሲያዘዋውሩ የተገኙ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለጸ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የተያዙት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 ለቡ ሙዚቃ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው ተብሏል።

ግለሰቦቹ የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-26732 አ.አ በሆነ ተሽከርካሪ በትላልቅ ፌስታል ካናቢስ የተባለውን አደንዛዥ ዕፅ ጭነው ሲያዘዋውሩ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ እና ባደረገው ክትትል ተሽከርካሪውን ጨምሮ አምስት ተጠርጣሪዎችን ከነኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር ማዋል እንደተቻለ ተገልጿል፡፡

ፖሊስ ለወንጀል መንስኤ በሆኑና አዋኪ ድርጊት በሚፈፀምባቸው ጫት መቃሚ ቤቶች እንዲሁም ቁማር ቤቶች ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት እርምጃ እየወሰደ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.