Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች በግል አልሚዎች እየለሙ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው።

አምባደሮች በፌዳ ዋቅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጎልድ የኢንዱስትሪ መንደርን ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር ባጫ ደበሌ፣ አምባሳደር ዳባ ደበሌ፣ አምባሳደር ሌንጮ ባቲ፣ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶችም ተሳትፈዋል።

የጉብኝታቸው አላማም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለተቀረው ዓለም ማስተዋወቅ፣ የሀገር ውስጥ አልሚዎችን ከተወከሉባቸው ሀገራት ባለሀብቶች ጋር ማስተሳሰርና የኢንቨስትመንት ዲፕሎማሲን ማጠናከር ነው ተብሏል፡፡

ጉብኝቱ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ነው እየተካሄደ የሚገኘው።

በአፈወርቅ እያዩ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.