በአማራ ክልል በየደረጃው ለሚገኙ የፀጥታ መዋቅር ስልጠና መሰጠት ተጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በአማራ ክልል ለሚገኙ የፀጥታ መዋቅር አመራሮች ግምገማዊ ስልጠና መሰጠት ተጀምሯል።
የስልጠናው አላማ የተዛነፉ አመለካከቶች በማረም ውስጣዊ አንድነትን በማጠናከር የህዝቡን ሰላም ማስጠበቅ እንደሆነም ተመላክቷል።
አሁን ላይ ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት የፀጥታ መዋቅሩ ጥንካሬውን በማስቀጠል ድክመቶችን ወደ ውስጥ በማየት በተጠናከረ መንገድ የህዝብ ሰላም በመጠበቅ ልማትን ማስቀጠል ይገባል ተብሏል።
ክልሉ ያለበትን ሁኔታ በማወቅ የጸጥታ መዋቅሩ ለአንድ አላማ በመሰለፍ ለህዝብ መቆም እንዳለበትም ተገልጿል።
የሰላምና ፀጥታ ወቅታዊ ግምገማዊ የስልጠና መድረክ ለ10 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ሲሆን÷በዚህም ፖሊስ፣ የማረሚያ ፖሊስ ፣ የሚሊሻ ጽ/ቤት አመራርና ባለሙያ እንዲሁም የሰላምና ጸጥታ አባላት ይሳተፋሉ፡፡