አቶ መላኩ አለበል ከዩኒዶ የሥራ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ምክትል ዳይሬክተር ጀነራል ፋቱ ሀይድራ ጋር ተወያዩ፡፡
በተጨማሪም በውይይቱ ላይ የዩኒዶ ኢትዮጵያ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
በውይይታቸውም÷ ስለ ዩኒዶ ድጋፍ ስኬቶች፣ በሥራ ሂደት ስላጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይ በሚደረጉ የትብብር ማዕቀፎች ላይ መክረዋል፡፡
ዩኒዶ አምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ እያደረገ ያለውን ጥረት አቶ መላኩ ማድነቃቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡
ዘርፉ በተሻለ ሁኔታ የሚጠበቅበትን ሀገራዊና ዓለም አቀፋዊ እድገት እንዲያሳካም ድርጅቱ ድጋፉን በይበልጥ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡