ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ከፍተኛ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ የሚገኘውን የምሥራቅ አፍሪካ አርብቶ አደሮች ኤክስፖን ጎብኝተዋል፡፡
ኤክስፖው “አርብቶ አደርነት የምሥራቅ አፍሪካ ኅብረ ቀለም” በሚል መሪ ሐሳብ በሚሊኒየም አዳራሽ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
በዛሬው ዕለትም የመንግሥት ከፍተኛ ሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በብልጽግና ፓርቲ ዋና ጽሕፈት ቤት የሚገኙ አመራሮች ኤክስፖውን ጎብኝተዋል፡፡