Fana: At a Speed of Life!

ከአንድ ሚሊየን በላይ ወጣቶችን የዲጂታል ክህሎት ባለቤት ለማድረግ ምክክር ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከጃይካ ጋር በመተባበር ከአንድ ሚሊየን በላይ ወጣቶችን የዲጂታል ክህሎት ባለቤት ለማድረግ በጋራ መክረዋል።
 
ሚኒስቴሩ ከጃይካ፣ ከሳፋሪኮም ኢትዮጵያና ከሱሚቶሞ ኮርፖሬሽን ጋር በመተባበር በአጭር ጊዜ 10 ሺህ እና በሂደት እስከ አንድ ሚሊየን ወጣቶችን የዲጂታል ክህሎት ላይ ለማሰልጠንና ተጠቃሚ ለማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
 
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ፕሮጀክቱ የዲጂታል ሥነ ምህዳርን በመገንባት የዲጂታል ኢኮኖሚን ለማጎልበት የሚያስችል የአሰራር ስርዓት ለመፍጠር የዲጂታል ክህሎት ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።
 
የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ለማሳደግ የዲጂታል ክህሎት ቁልፍ ነው ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከጃይካ ጋር እየተሰሩ ያሉ አበረታች ስራዎችን አድንቀዋል፡፡
 
በቀጣይ ይበልጥ በዲጂታል ቴክኖሎጂው ላይ ትኩረት በማድረግ የሀገራዊ ኢኮኖሚውን ሊያበለፅጉ የሚችሉ ውጤቶችን ለማምጣት በትብብር መስራቱ ወሳኝ ነው ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
 
የጃይካ ዲኤክስላብ ኃላፊ ዩሺ ናጋኖ በመላው ኢትዮጵያ 10 ሺህ የዲጂታል ክህሎት ያላቸው ወጣቶችን በአጭር ጊዜ በማብቃት በቀጣይ ሚሊየኖች ላይ አቅም ለመፍጠር እንደሚሰራ ገልፀዋል።
 
 
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.