Fana: At a Speed of Life!

የመሥተዳድር ምክር ቤቱ በተሻሻሉ ልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳለፈ

አዲስ አበባ፣ ጥር 22፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የመሥተዳድር ምክር ቤት በተሻሻሉ ልዩ ልዩ ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ በመወሰን ለክልሉ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መራ፡፡

አዲሱን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሕገ-መንግሥት መሠረት በማድረግ በተሻሻሉ ልዩ ልዩ 11 ረቂቅ አዋጆች ላይ በመወያየት በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው የመሥተዳድር ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጆቹ ለክልሉ ምክር ቤት መርቷል።

ለምክር ቤት የተመሩት ረቂቅ አዋጆችም÷ የታክስ አስተዳደር አዋጅ፣ የገቢ ግብር አዋጅ፣ የቴንብር ቀረጥ አዋጅ፣ ተርን ኦቨር ታክስ አዋጅ፣ የመንግሥት ሠራተኞች አዋጅ እና የፍርድ ቤቶች አዋጅ መሆናቸውን የርዕሰ መሥተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

የዳኝነት አስተዳደር አዋጅ፣ የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ አዋጅ፣ የማረሚያ ቤቶች አሥተዳደር ኮሚሽን አዋጅ፣ ሥነ-ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ እንዲሁም የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባዔ አዋጅ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.