በኦሮሚያ ክልል 3 ሺህ 764 ትምህርት ቤቶች ተገንብተዋል ተባለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ስድስት ወራት 3 ሺህ 764 የቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በቢሮው የእቅድና በጀት ዝግጅት ዳይሬክተር ሃሰን እንድሪስ÷ በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ያለውን የትምህርት ቤቶች ተደራሽነት ለማሳደግ በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡
በተለይም የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል እና አስፈላጊ ግብዓቶችን ለማሟላት በቅንጅት ተሰርቷል ብለዋል፡፡
በዚህ መሰረትም በሕብረተሰቡ ተሳትፎ 4 ሺህ 574 ቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶችን ለመገባንት ታቅዶ 3 ሺህ 764 ትምህርት ቤቶች መገንባታቸውን ነው የገለጹት፡፡
በሌላ በኩል 3 ሺህ 410 ከደረጃ በታች የሆኑ ትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል ታቅዶ 4 ሺህ 418 ትምህርት ቤቶችን በማሻሻል ከዕቅድ በላይ ማሳካት መቻሉን ጠቁመዋል፡፡
በመላኩ ገድፍ