የሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ምክር ቤት 6ኛ ዘመን 6ኛ ዙር መደበኛ ጉባኤውን ማካሄድ ጀምሯል፡፡
ምክር ቤቱ በጉባኤው የምክር ቤቱን የ6ኛ ዘመን 1ኛ አመት 1ኛ መደበኛ ጉባኤ ቃለ ጉባኤን መርምሮ ያፀድቃል።
የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ የክልሉን መንግስት የ6 ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ እያቀረቡ ነው፡፡
በተጨማሪም ምክር ቤቱ በተለያዩ ጉዳዮች ላይ እንደሚመክር የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡