Fana: At a Speed of Life!

84ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 84ኛው የአገው ፈረሰኞች ማኅበር ዓመታዊ በዓል በእንጅባራ ከተማ እየተከበረ ነው።

በዓሉ”የሰላም አርበኝነት ለወንድማማችነት”በሚል መሪ ሀሳብ ነው በተለያዩ ዝግጅቶች እየተከበረ የሚገኘው፡፡

በአከባበር ሥነ- ሥርዓቱ የአማራ ክልል ም/ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዱ ሁሴን፣ የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ፣ ሌሎች የክልሉ የሥራ ሃላፊዎች እና የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

የአገው ፈረሰኞች ማኅበር የብሔረሰቡ አባቶች ከሌሎች አርበኞች ጋር በመተባበር የጣልያንን ወራሪ ጦር ዓድዋ ላይ ድል መቀዳጀታቸውን ለመዘከር በየዓመቱ ጥር 23 የሚከበር በዓል ነው፡፡

አሁን ላይም በብሔረሰብ አስተዳደሩ የሚገኙ የባህል ቡድን አባላት የተለያዩ ባህላዊ ጭፈራዎችን እያሳዩ መሆኑን የአዊ ዞን ኮሙኒኬሽን መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.