Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ ከዩኒዶ ጋር የ28 ሚሊየን ዶላር ፕሮጀክት ስምምነት ተፈራረመች

አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ጋር የ28 ሚሊየን ዶላር የፕሮጀክት ስምምነት ፊርማ ተፈራርማለች፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው እና የዩኒዶ ኢትዮጵያ ተዋካይ ሚስተር ቻሌብሮ ኦርሊያ ፓትሪዚያ በጋራ ፈርመውታል፡፡

ስምምነቱ በሚቀጥሉት አምስት አመታት በኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ልማትን ለመደገፍ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

በተጨማሪም የፕሮጀክት ስምምነቱ የኢንዱስትሪ ተረፈ ምርቶችን መልሶ ጥቅም ላይ ለማዋል እንዲሁም በጨርቃ ጨርቅና አልባሳት ኢንዱስትሪ ውስጥ ያለውን ተቋማዊ አቅም ለማሳደግ ይውላል ተብሎ ይጠበቃል።

የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታዋ በስምምነቱ ወቅት እንዳሉት÷ መንግስት የማኑፋክቸሪንግ ዘርፉን ለማሳደግና ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን ለመተካት እየሰራ ይገኛል፡፡

በመሆኑም ዩኒዶ ኢትዮጵያ በምታደርገው የኢንዱስትሪያላይዜሽን ጉዞ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት መግለፃቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.