ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባላት ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ትብብር አጠናክራ ትቀጥላለች- አቶ ማሞ ምህረቱ
አዲስ አበባ፣ ጥር 23፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ ከብሪክስ አባል ሀገራት ጋር ያላትን ኢኮኖሚያዊ ግንኙነት አጠናክራ እንደምትቀጥል የብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ ገለጹ፡፡
በአቶ ማሞ ምህረቱ የተመራ ልዑክ በሩሲያ እየተካሄደ በሚገኘው የመጀመሪያው የብሪክስ አባል ሀገራት ስብሰባ ላይ እየተሳተፈ ነው፡፡
ከስብሰባው ጎን ለጎንም አቶ ማሞ ከሩሲያ ፌዴሬሽን፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ሕንድ፣ ብራዚል እና ቻይና ተወካዮች ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡
በውይይቱም ኢትዮጵያ ከሀገራቱ ጋር በኢኮኖሚ ትብብር መስኮች ግንኙነቷን ለማሳደግ ቁርጠኛ እንደሆነች አቶ ማሞ ተናግረዋል፡፡
በንግድ፣ ኢንቨስትመንት እና በቱሪዝም መስኮች ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሚሰሩ የሀገራቱ ተወካዮች መግለጻቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡