የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶችን የሰረቁ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማቶች ላይ ስርቆት የፈጸሙ ግለሰቦች በፅኑ እስራት ተቀጡ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ስድስት ወራት በኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ 20 ወንጀለኞችን ከ2 ዓመት እስከ 12 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት መቀጣታቸውን አስታውቋል፡፡
የቅጣት ውሳኔ የተላለፈባቸው ወንጀለኞች የኤሌክትሪክ መሠረተ-ልማት ስርቆት የፈፀሙ፣ በህገ ወጥ መንገድ ቆጣሪ ያስገቡ፣ በምሰሶና በኤሌክትሪክ መስመር ላይ ጉዳት ያደረሱ እንደሆኑም ነው የተገለጸው፡፡
በተጨማሪም ተቋሙ በንብረትና መሰረተ-ልማቶች ላይ ጉዳት ያደረሱ 47 ጉዳት አድራሾች ላይ ማስጠንቀቂያ በመስጠት 8 ሚሊየን 239 ሺህ 712 ብር መጠየቁም ተነግሯል፡፡
ከዚህ ዉስጥ 5 ሚሊየን 526 ሺህ 407 ብር ለተቋሙ ገቢ እንዲሆን ማድረግ መቻሉም ነው የተነሳው፡፡
የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅ በኤሌክትሪክ ዉዝፍ ዕዳ ክፍያ፣ በውል ማስፈጸሚያ ዋስትና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩሩ ክሶችን በመመስረት 66 ሚሊየን 634 ሺህ 446 ብር ለተቋሙ ገቢ ማድረግ ተችሏል ተብሏል፡፡
የኃይል ስርቆት በፈፀሙ 13 ግለሰቦች ላይ ክስ በመመስረትና ማስጠንቀቂያ በማሰጠት 2 ሚሊየን 194 ሺህ 324 ብር እንዲከፍሉ ማድረግ መቻሉም ነው የተጠቀሰው፡፡
ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት የገንዘብ መጠናቸው 1 ቢሊየን 124 ሚሊየን 730 ሺህ 417 ብር የሆኑ 509 ክሶች ላይ ክትትል ሲያደርግ መቆየቱንም አንስቷል፡፡
ከዚህ ውስጥ የገንዘብ መጠናቸው 98 ሚሊየን 142 ሺህ 911 ብር የሆኑ 120 ክሶች ውሳኔ እንዲያገኙ መደረጉን ከተቋሙ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!