ስፓርት

የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ዛሬ ይደረጋሉ

By Mikias Ayele

February 02, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በ34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ናይጄሪያ ከአንጎላ እንዲሁም ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከጊኒ ይገናኛሉ፡፡

ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረገው ጨዋታ÷ ናይጄሪያ ከአንጎላ የሚያደርጉት ጨዋታ ምሽት 2፡00 ሠዓት ላይ በአቢጃን ፌኪክስ ሆፌት ስታዲየም ይደረጋል፡፡

ሁለቱ ቡድኖች በታሪክ 10 ጊዜ ተገናኝተው ናይጄሪያ በሦስቱ  እንዲሁም አንጎላ በሁለቱ ሲያሸንፉ÷ አምስቱን ጨዋታዎች ደግሞ አቻ ተለያይተዋል፡፡

በተመሳሳይ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 5፡00 ሠዓት ላይ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ከጊኒ በአላሳን ኦታራ ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ግብፅን እንዲሁም ጊኒ ደግሞ ጊኒ ቢሳውን በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀላቸው ይታወቃል፡፡