Fana: At a Speed of Life!

በምጣኔ ኃብትና በዲፕሎማሲ መስክ ለተመዘገቡ ውጤቶች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍቢ ሲ) በ2016 በጀት የመጀመሪያ ስድስት ወራት እንደ ሀገር በምጣኔ ኃብትና ዲፕሎማሲ መስክ ለተመዘገቡ ውጤቶች የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ማድረጉን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት የ2016 የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ተቋማት የጋራ ጉባዔውን በአዳማ ከተማ እያካሄደ ነው።

በመድረኩ ባለፉት ስድስት ወራት በሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራት በጋራ የሚገመገምበት ነው።

የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት÷ በዚህ ዓመት በየደረጃው የሚገኘው የሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ በተደራጀ መንገድ ወደ ሥራ የገባበት ነው።

ባለፉት ስድስት ወራት መንግሥት ትኩረት ባደረገባቸው አምስቱ የምጣኔ ኃብት ምሶሶዎች በርካታ አመርቂ ሥራዎች መከናወናቸውን ጠቁመዋል።

የሕግ የበላይነትና መልካም አስተዳደር በማስፈን፣ አዎንታዊና ዘላቂ ሰላም በማረጋገጥ እንዲሁም በዲፕሎማሲና ሌሎች ዘርፎችም አበረታች ሥራዎች ተከናውነዋል ብለዋል።

በእነዚህ ዘርፎች እንደ ሀገር ለተመዘገቡ ውጤቶች የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዘርፉ ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል ነው ያሉት።

ያም ሆኖ የሐሰተኛ መረጃዎችን ጨምሮ ሌሎች ተግዳሮቶችም እንደነበሩ ጠቅሰው÷ በቀጣይ የተሻለ ለመሥራት በረባረብ እንደሚጠይቅ ማስገንዘበቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.