Fana: At a Speed of Life!

ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር) ከግሎባል ግሪን ግሮዝ ኢንስቲትዩት የኢትዮጵያ ተወካይ ዳንኤል ኦግቦናያ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም የግብርና ዘርፉን ምርታማነት ለማሣደግና የአርሶ አደሩን የአፈር ጤንነት ችግር ለመፍታት በሚያስችሉ ድጋፎች ላይ መክረዋል፡፡

የግብርና ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሣደግ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑም ተገልጿል፡፡

ተግባራዊ የተደረጉ በርካታ የግብርና ኢኒሼቲቮች ለዘርፉ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከቱ መሆኑን ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

የስንዴ፣ አረንጓዴ ዐሻራና የሌማት ትሩፋት ኢኒሼቲቮች ውጤታማ በሆነ መንገድ እየተተገበሩ መሆናቸውንም ገልጸዋል፡፡

የግብርናው ልማት በታሰበው ፍጥነት እንዲሄድ የልማት አጋሮች ትልቅ ድርሻ እንዳላቸው ገልጸው÷ እነዚህና ሌሎች የግብርና ልማቶችን መደገፍ እንደሚገባ ማስገንዘባቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል፡፡

የግብርና ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሣደግ የተፈጥሮ ሃብት ጥበቃ ሥራ ላይ በርካታ ሥራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡

የአረንጓዴ ዐሻራ ትግበራ ለግብርና ምርታማነት ዕድገትና የዓየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል ድርሻው የጎላ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.