ሚትስቡሺ ኩባንያ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና መሰማራት እፈልጋለሁ አለ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ዓለም ዓቀፉ የመኪና አምራች ኩባንያ ሚትስቡሺ በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ከትሬዲንግ ጋር በተያያዙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ላይ መሳተፍ እንደሚፈልግ አስታውቋል፡፡
የሚትስቡሺ ኩባንያ ሥራ አስኪያጅ ሺግዮሺ÷ የሐዋሳ፣ አዳማ እና ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝታቸው በኋላም ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ዘርፍ ምክትል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዘመን ጁነዲ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸውም በድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጣና ከትሬዲንግ ጋር የተያያዙ ኢንቨስትመንቶች ላይ መሰማራት እንደሚፈልጉ አስታውቀዋል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘም ኩባንያው ለኢንቨስትመንቱ የሚረዱ ቅድመ ጥናቶችን ማከናወን ይፈልጋል ብለዋል፡፡
አቶ ዘመን በበኩላቸው÷ ሚትስቡሺ ለትሬዲንግ ኢንቨስትመንት የሚረዳውን ጥናት እንዲያደርግና በቢዝነሱ እንዲሰማራ ኮርፖሬሽኑ ድጋፍ እንደሚያደርግ ማረጋገጡን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!