የትግራይ ክልል 100 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ወደ ክልሉ መግባቱን ገለጸ
አዲስ አበባ፣ ጥር 24፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) ለምርት ዘመኑ ከተጠየቀው የአፈር ማዳበሪያ ውስጥ 100 ሺህ ኩንታሉ ወደ ክልሉ መግባቱን የትግራይ ክልል ገለፀ።
ለ2016/17 ምርት ዘመን በክልሉ ያስፈልጋል ተብሎ ከተጠየቀው 900 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ውሥጥ ነው 100 ሺህ ኩንታሉ ወደ ክልሉ የደረሠው።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አሥተዳደር እርሻና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ምክትል ኃላፊ አለምብርሃን ሃሪፈዮ ለፋና ብሮድካሥቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ ለምርት ዘመኑ ግብዓት ቀድሞ መድረሡ የአርሶ አደሩን ጥያቄ ለመመለሥ ወሳኝ ነው።
ቀሪው ግብዓት ደግሞ በወቅቱ እንዲደርሥ ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በቅንጅት እየተሠራ ነው ያሉት ምክትል ኃላፊው፥ ተሽከርካሪዎች ቀሪውን ግብዓት በመጫን ወደ ክልሉ እንቅሥቃሴ ጀምረዋል ሲሉም ተናግረዋል።
የግብርና ግብዓቶችን ለክልሉ ቀድሞ በማቅረብ ረገድ የግብርና ሚኒስቴርን ያመሠገኑት አቶ አለምብርሃን ሃሪፈዮ፥ ሌሎች የግብርና ልማት ሜካናይዜሽን መሣሪያዎች ለአርሶ አደሩ እንዲደርሡ በማድረግ በክልሉ የተከሠተውን ድርቅ ለመከላከል ለሚሠራው ሥራ አበርክቶ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ነው የገለጹት።
በሰለሞን ይታየው
#Ethiopia
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!