ስፓርት

ዛሬ ሁለት የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ይደረጋሉ

By ዮሐንስ ደርበው

February 03, 2024

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) 34ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ዛሬ ቀጥለው ሲካሄዱ ማሊ ከኮትዲቯር እንዲሁም ኬፕ ቨርዴ ከደቡብ አፍሪካ ይገናኛሉ፡፡

ወደ ግማሽ ፍጻሜ ለማለፍ በሚደረገው ፍልሚያ ማሊ ከአስተናጋጇ ኮትዲቯር ምሽት 2፡00 ሠዓት ላይ ጨዋታቸውን እንደሚያደርጉ የወጣው መርሐ-ግብር ያስረዳል፡፡

እንዲሁም ኬፕቨርዴ ከደቡብ አፍሪካ ምሽት 5፡00 ሠዓት ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ተጠባቂ ነው፡፡

ትናንት በተካሄዱ የመጀመሪያ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ናይጄሪያ አንጎላን 1 ለ 0 እንዲሁም ዴሞክራቲክ ኮንጎ ጊኒን 3 ለ 1 በመርታት ወደ ግማሽ ፍጻሜ ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/ ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!