Fana: At a Speed of Life!

በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ልማትና አብሮነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፣ ጥር 25፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ የሰላም ግንባታ፣ ዘላቂ ልማትና አካባቢያዊ አብሮነት ላይ ያተኮረ ጉባዔ በድሬዳዋ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ጉባዔው “ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሶማሊ ላንድ መካከል ቀጣናዊ ትስስርን ለመፍጠር፣ ለሰላም ግንባታና ሁሉን አቀፍ ልማት ለማረጋገጥ ያላቸው ሚና በሚል መሪ ሐሳብ ላይ ነው እየተካሄደ የሚገኘው፡፡

አሁን ላይም በኢትዮጵያ፣ ጅቡቲ እንዲሁም ሶማሊ ላንድ መካከል ለሚኖረው ትብብር እና የሰላም ግንባታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መወጣት በሚገባቸው ሚና ላይ ውይይት እየተደረገ ነው።

በአፍሪካ ቀንድ ስላለው የሰላምና የጸጥታ ሁኔታ፣ የጋራ ዕድሎችና ስጋቶች፣ ቀጣናዊ ትስስር፣ ዘላቂ ልማትና የሰላም ግንባታ ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች በጉባዔው ላይ እንደሚቀርቡም ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም በአካባቢው የሚፈጠሩ ግጭቶችን ለመፍታት ባህላዊ የግጭት መፍቻ ሥርዓቶችና ተቋማት ባላቸው ሚና ላይ ያተኮሩ ጥናታዊ ጽሑፎች በምሁራን ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል ተብሏል።

የሰላም ሚኒስቴር ከድሬዳዋ፣ ጅግጅጋ፣ ቀብሪ ደሀር፣ ሐሮማያ፣ ሠመራ እንዲሁም ሀርጌሳ እና ጅቡቲ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር ጉባዔውን ማዘጋጀታቸው ተገልጿል፡፡

በቅድስት አባተ

#Ethiopia

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision
ኢንስታግራም፦ https://www.instagram.com/fana_television/
ቲክቶክ፦ https://www.tiktok.com/@fana_television በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.